ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ አቶ ነሲቡን አዲስ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሾመ

Date:

ዩኒሊቨር ኢትዮጵያ አቶ ነሲቡ ተመስገንን አዲስ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ከመጋቢት 23 ቀን 2017 ጀምሮ እንዲያገለግሉ መሾሙን አስታወቀ። 18 ዓመታትን ያስቆጠረ የሥራ ልምድ ያላቸው አቶ ነሲቡ፣ ከዚህ ውስጥ ግማሽ ያህሉን በዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ አገልግለዋል።

ነሲቡ በዩኒሊቨር ኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ የድርጅቱን ሽያጭ እና የገበያ አቋም በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ቁልፍ ሚና መጫወታቸውን ኩባንያው ገልጿል ።

“ምርታማነትን ያማከለ እድገት፣ የሰው ኃይል ማብቃት እና የላቀ አፈጻጸም ቅድሚያ ትኩረቴ ናቸው” ያሉት አቶ ነሲቡ፣ “የዩኒሊቨርን እሴቶች እና ባህሪያት በመጠበቅ ተገቢውን የቁጥጥር እና የአስተዳደር ስርዓት በመዘርጋት ይህን እውን ለማድረግ ቁርጠኛ ነኝ” ብለዋል።

ከኩባንያዉ ለካፒታል በተላከዉ መግለጫ አቶ ነሲቡ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በማርኬቲንግ ማኔጅመንት የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተማሩ ሲሆን፣ በዩኒሊቨር የሚሰጠውን የአፍሪካ ሊደርሽፕ አክስሌረተር ፕሮግራምንም አጠናቀዋል።

መቀመጫው በእንግሊዝ ሀገር የሆነው የአለም አቀፉ ዩኒሊቨር በኢትዮጵያም ላለፉት ስምንት ዓመታት እንደ ላይፍቦይ፤ ኦሞ እና ክኖር የመሳሰሉ የግልና የጋራ ንጽህና መጠበቁያዎች እንዲሁም ምግብ ነክ ምርቶችን እያቀረበ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ አምራች ድርጅት መሆኑ ይህ ።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...