“አረጋውያንን እመግባለሁ ጤንነቴን እጠብቃለሁ!” በሚል መሪ ቃል የሜሪጆይ ሩጫ ተካሄደ

Date:

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ” አረጋውያንን እመግባለሁ ጤንነቴን እጠብቃለሁ በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 5 ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄደ።

መነሻውንና መድረሻውን አዲሱ ፒኮክ መናፈሻ አከባቢ ባደረገው 5ኪሎ ሜትር ሩጫ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን፣ የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ቆንጅት ደበላ፣ የሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ መስራች ሲስተር ዘቢደር ዘውዴን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ ታዋቂ አርቲስቶች፣ የስፖርት ቤተሰቦች፣ ወጣቶች፣ ታዳጊዎች እና የከተማው ነዎሪዎች በስፋት ተሳትፈውበታል።

ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ ላለፉት 31 ዓመታት ለተቸገሩ ህጻናት እና አረጋውያን የሰብአዊ ድጋፍ ሲያካሂድ መቆየቱን የገለፁት ሲስተር ዘቢዳር በቀጣይም ይህን ድጋፉን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች እና ተቋማት ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...