ጣና ነሽ ጀልባ ከ3 ወራት በኋላ ጎርጎራ ትደርሳለች

Date:


ጣና ነሽ ጀልባ ከጂቡቲ ዶራሌ ፈርጀ-ብዙ ወደብ ወደ አገር ቤት ዛሬ ጠዋት ጉዞ ጀምራለች። በአማካኝ ከ3 ወራት በኋላ ጎርጎራ ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።

የጣና ነሽ ጀልባ 150 ሜትሪክ ቶን ክብደት የምትመዝን፣ 38 ሜትር ርዝመት ያላት እና 200 ተሳፋሪ የመያዝ አቅም ያላት ሲሆን ለመዝናኛ አገልግሎት በመጠቀም እያደገ ያለው የቱሪዝም ዘርፍ ላይ ትልቅ አስተዋጾ የምታበረክት ይሆናል።

ጀልባዋ ከጅቡቲ ተነስታ በዲኪል-ካላፊ መንገድ  የምትንቀሳቀስ ሲሆን፣ በአማካይ ከ7 ቀናት በኋላ ኮሪደሩን ታቋርጣለች ተብሎ ይጠበቃል። ለጉዞ የሚሆን የዝቅተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ የሃይል ተሸካሚ መስመሮች በኮሪደሩ የሚቋረጡና ተለዋጭ መንገድ የተዘጋጀላቸው ሲሆን፣ ሁለት ተጨማሪ ጎታች ተሽከርካሪዎችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ተመድቦ ከጀልባዋ ጋር ጉዞ ጀምሯል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት በዛሬ ዕትሟ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ነሔሴ 16 2018 ዓ.ም ገበያ...

ቱርክ ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ አወጣች

ቱርክ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ላይ ዓለም አቀፍ...

በመቀለ የሚካሄደው የአሸንዳ በዓል የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ተሰረዘ

በትግራይ በርካታ ታዳሚ በሚገኝበት በየዓመቱ የሚከበረው የአሸንዳ ባህላዊ በዓል...

የኢትዮጵያ ፖስታ 3 ሺሕ የሚጠጉ ቅርንጫፎቹን ወደ ባንክ ኤጀንትነት ለመቀየር እንቅስቃሴ ጀመረ

የኢትዮጵያ ፖስታ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ 3 ሺሕ በሚጠጉ ቅርንጫፎቹ...