ኤን.ኤም. ሲ ሪል ስቴት የማዕድ ማጋራት እና 45 መኖሪያዎችን ሠርቶ እያስተላለፈ ይገኛል

Date:

በቤቶች ልማት ዘርፍ ላይ ተሠማርቶ የሚገኘው ኤን.ኤም ሲ ሪል ስቴት የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ 1ሺህ አቅመ- ደካሞችና ወላጅ አልባ ለሆኑ ህጻናት የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም፣ 100 ወላጅ አልባ ህፃናትን ሲደግፍ እንደነበር ይታወቃል፡፡

የኤን. ኤም. ሲ ሪል ስቴት ባለቤትና ሥራ አስኪያጅ አቶ መሠረት መኮንን እንደተናገሩት ድርጅታቸው የመረዳዳት እና አንዱ ሌላውን ደግፎ የመኖር ባህል እንዳለው ገልፀው በዘንድሮው የትንሳኤ በዓል አቅመ- ደካሞችና ወላጅ አልባ ህጻናት በአሉን ደስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ በማሰብ ነው ድጋፍ ያደረግነው ብለዋል፡፡

ድርጅቱ ቱሉ ዲምቱ በሚገኘው የኤን. ኤም. ሲ የግንባታ ቦታ ላይ የርክክብ ስነስርአቱና የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብሩ አከናውነዋል።

አቶ መሰረት ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባቀረበላቸው ጥሪ መሠረት ለአቅመ-ደካሞችና ለድሀ ድሀ ነዋሪዎች የሚያገለግሉ ቤቶች ሰርተው አስረክበው እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ከዚህም ባሻገር፣ ድርጅቱ የሸገር ዳቦ ሱቆችን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ በሚገኙ 13ቱም ወረዳዎች እንዲገነባ አድርጓል፡፡

በተጨማሪም በ90 ቀን ሰው ተኮር ፕሮጀክት ባለሀብቶችን በማስተባበር አቶ መሠረት ለሀገር የሚጠቅም በጎ ተግባር ማከናወን መቻላቸውንም ተናግረዋል።

ኤን ኤም ሲ ሪል ስቴት በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን የቤት ችግር ለማቃለል በአቃቂ 11 ነጥብ 5 ቢልዮን ብር በሚገመት ካፒታል የተጀመረው የድርጅቱ የግንባታ ስራ 1ሺህ ቤቶችን ሰርቶ የሚያጠናቅቅ ይሆናል ተብሏል።

ድርጅቱ 45 መኖሪያዎችን ሠርቶ ለቤት ፈላጊዎች እያስተላለፈ ይገኛል ።

ድርጅቱ ለአቅመ ደካሞችን እና ወላጅ አልባ ህጻናት ለመደገፍ ባዘጋጀው ሥነ-ስርአት ላይ የመንግስት ሀላፊዎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

ቲክ ቶ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...