በሴቶች የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ወደ ፈረንሳይ ተጉዞ ሊዮንን 4 ለ 1 አሸንፏል።
በሊዮን በተደረገው ጨዋታ ማሪዮና ካልደንቲ ፣ አሊሲያ ሩቶ ፣ ኬትሊን ፎርድ እና ኢንድለር በራሷ መረብ ላይ የአርሰናልን ግቦች አስቆጥረዋል።
ዱሞናይ የሊዮንን አንድ ግብ ያስቆጠረች ተጫዋች ሆናለች።
በመጀመርያው ጨዋታ በሜዳው 2 ለ 1 ተሸንፎ የነበረው አርሰናል ውጤቱን ቀልብሶ በድምር ውጤት 5 ለ 3 በማሸነፍ ከ18 አመት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆኑን አረጋግጧል።
በሌላ የግማሽ ፍጻሜ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ቼልሲን 4 ለ1 አሸንፏል።
በመጀመርያው ጨዋታም በተመሳሳይ 4 ለ 1 ያሸነፈው ባርሴሎና በድምር ውጤት 8 ለ 2 በማሸነፍ ለዋንጫ ጨዋታ ደርሷል።
በፍጻሜው አርሰናል ከባርሴሎና በሊዝበን የሚገናኙም ይሆናል።
በአንተነህ ሲሳይ
