ሦስት ጊዜ ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች እርምጃ እንደሚመወሰድባቸው ተገለጸ

Date:

በተ

በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከ25 በመቶ በታች ውጤት በሚያስመዘግቡ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚመወሰድ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ይህን ያሉት የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ከቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ጋር በተወያየበት መድረክ ላይ ነው፡፡

በዚሁ ጊዜ ፕሮፌሰር ብርሃኑ “ዩኒቨርሲቲዎች ሰው እውቀትና እውነት ፈልጎ የሚመጣባቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል” ብለዋል።

አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሯቸው ተማሪዎች ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግን ዋና ተግባራቸው አድርገው መሥራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በዚህ ረገድ በተከታታይ ሦስት ጊዜ በተመራቂ ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ውጤት ከ25 በመቶ በታች ካስመዘገቡ በትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን በኩል እርምጃ እንደሚወሰድ አመላክተዋል።

የዩኒቨርሲቲ አመራሮች በብቃትና በችሎታ እንዲመደቡ እየተደረገ መሆኑን አንስተው፤ አሰራራቸውን ለማዘመንም የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ማሰልጠኛ ተቋም ለማቋቋሞ እየተሠራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በበኩላቸው፤ “ዩኒቨርሲቲዎች በተሰጣቸው የተልዕኮ መስክ ልየታ መሠረት ትኩረት አድርገው ሊሠሩ ይገባል” ብለዋል።

አክለውም ዩኒቨርሲቲዎች የእውቀትና የሥነ ምግባር ፋና በመሆናቸው ተማሪዎቻቸውን ማብቃት ላይ ትኩረት አድርገው ሊሰሩ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...