በዋሽንግተን ዲሲ ለሚኖሩና ለሚሰሩ አስቸኳይ መልዕክት

Date:

ከትላንት ጀምሮ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ የንግድ ተቋማት፣ በተለይም በሬስቶራንቶችና በምግብ አድራሽ (Food Delivery) ድርጅቶች ላይ የመኖርያ ወይም የስራ ፍቃድ የሌላቸውን ሰወች የማፈስ መጠነ ሰፊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑ ተነግሯል።

ለሰራተኞች፡
የስራ ፈቃድ፣ የመኖርያ ፈቃድ፣ ማመልከቻችሁ ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ደረሰኝ ወይም ሌላ ተገቢ ህጋዊ መረጃ ይዛችሁ መንቀሳቀስ አትርሱ።

በቁጥጥር ስር ከዋላችሁም ያለመናገር መብታችሁን መጠቀም፣ ምንም አይነት ሰነድ ላይ አለመፈረም እና ጠበቃችሁን ማነጋገር አትርሱ።

የሬስቶራንት ባለቤቶች/ ቀጣሪወች፡
የስደተኛ ጉዳይ አካላት ሲመጡ የሚጠይቁት፣ “ሰራተኞቻችሁ እዚህ ሃገር ስራ የመስራት ፈቃድ እንዳላቸው አጣርታችኋል ወይ?” የሚል ጥያቄ ነው። ይህ ማለት ደግሞ በቅጥር ሂደት ላይ I-9 የሚባል የሰራተኛ ፈቃድ ማጣርያ ሰነድ (Employment Eligibility Verification) ማስሞላታችሁን እርግጠኛ ሁኑ። ይሄ ፎርም ተሞልቶ ከሰራተኞቹ ማህደር ውስጥ መቀመጥ አለበት።

ማስታወሻ፡ ይሄ መረጃ ግንዛቤን ለማስፋት የቀረበ እንጂ የህግ ባለሞያን ምክር የሚተካ አለመሆኑን ከወዲሁ መግለጽ እወዳለሁ።
በአበበ ፈለቀ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...