የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጌታቸው መንግስቴ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 23 አውሮፕላን ማረፊያዎች መደበኛ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም 22 የአነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያዎች በባለስልጣኑ እውቅና አግኝተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው ፡፡
በፌደራል መንግስት አምስት ኤርፖርቶች እየተገነቡ እንደሚገኙ ጠቁመው ነባሮቹ ላይም የማስፋፊያና የማሻሻያ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛል ።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን ከፌዴራል መንግሰት በተጨማሪ የክልል መንግስታት፣ የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ባለሀብቶች ኤርፖርት እንዲገነቡ እና እንዲያስተዳድሩ የሚያስችል መመሪያ ማውጣቱንም አስታውቀዋል ።
በዚሁ መሰረት 32 አዳዲስ አነስተኛ አውሮፕላን ማረፊያዎችን ለመገንባት ጥያቄ የቀረበ ሲሆን ባለስልጣኑ ቦታው ድረስ በመሄድ መረጣ ማካሄዱን ተናግረዋል ።
የቅዳሜገበያ….ፌስቡክ ገጽ
የቅዳሜገበያ….ቴሌግራም
የቅ
