ከሦስት አመት በፊት ደሞዝ መክፈል ያልቻለው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ፣ ዛሬ ከአንድ ሺህ 500 ኩንታል የቀን ምርት ወደ ሰባት ሺህ ኩንታል በቀን ለማደግ መቻሉን ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል፡፡
ፋብሪካው ፈታኝ ዓመታትን በማለፍ፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 8.7 ቢሊዮን ብር ገቢ አስመዝግቧል ብለዋል።
“የወንጂ ሸዋ ስኳር ፋብሪካ ስኬት፣ ተሀድሶ እንዴት እንደሚሰራ የሚያሳይ ቋሚ ኤግዚቢሽን ነው” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት በX ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።
በተጨማሪም ለ14 ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የብዙዎች ትዝታ፣ ደስታ ከረሜላ፣ ፋብሪካው ዳግም ማምረት መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
