“ዓላማዬን አሳክቼ ህልሜን እየኖርኩ ስለሆነ ደስተኛ ነኝ” ሎዛ አበራ

Date:

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን አምበል እና ለአሜሪካው ዲሲፓወር ክለብ የምትጫወተው ሎዛ አበራ ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 (ኢቢሲ) ጋር በወቅታዊ አቋሟ እና በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ቆይታ አድርጋለች።

ኢትዮጵያዊቷ ተጫዋች ሎዛ አበራ ባለፈው ሳምንት ክለቧ ዲሲ ፓወር ትሪኒቲን 3ለ2 በረታበት ጨዋታ ተቀይራ ገብታ ሁለት ጎሎችን አስቆጥራለች።ዲሲ ፓወር 2ለ0 እየተመራ በነበረበት በዚህ መርሃግብር ጎል ማስቆጠሯ የበለጠ እንዳስደሰታት እና ለቡድኑ የማጥቃት እንቅስቃሴ መለወጥ ምክንያት መሆኗ ለእሷም ልዩ ታሪክ እንደሆነ ተናግራለች።

ክለባቸው በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ አጋማሽ  የተሻለ እንደሆነ እና በመጀመሪያው ዙር  እንደቡድን ለመግባባት እና ለመዋሃድ አስቸጋሪ እንደነበር የምትገልፀው ተጫዋቿ. የአሰልጣኝ ቅያሪ መደረጉ ብሎም እሷን ጨምሮ የቡድኑ ስብስብ በአዳዲስ ልጆች የተገነባ መሆኑ ፈተናቸውን ከፍ እንዳደረገው አስረድታለች።

«ውድድሩ በጣም ጥሩ ነው ዓመቱን ልንጨርስ አራት ጨዋታ ይቀረናል። እንደቡድን በጣም ለውጥ ያሳየንበት እንዲሁም  የተሻሉ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነው በዛ ደስተኞች ነን የተሻለ ስራንም እየሰራን ነው።» ብላለች።

በአሜሪካ እያሳለፈች በምትገኘው ህይወት ደስተኛ መሆኗን የምትገልፀው ሎዛ አበራ ሁሌም ራሷን ለማሻሻል ከቀን ወደ ቀን እንደምትጥር ታሰምራለች።

« በህይወቴም በስራዬም ደስተኛ ነኝ። ዓላማዬን አሳክቼ ህልሜን እየኖርኩ ስለሆነ በጣም ደስተኛ ነኝ።» ያለችው ተጫዋቿ መጀመሪያ አካባቢ ከቋንቋ እና ከአኗኗር ባህል አንፃር ተቸግራ እንደነበር አንስታ አሁን ሁኔታዎች ተቀይረው ጥሩ ሁኔታ ላይ እንደምትገኝ ተናግራለች። «እግርኳስ ራሱን የቻለ ቋንቋ ነው» ስትልም ሀሳቧን አጠናክራለች።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...