ምርጫ ቦርድ ሁለተኛ ዙር የምርጫ ጣቢያዎችን   በዲጂታል ሲስተም መመዝገብ  ጀመረ

Date:

የኢትዯጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንደ አዲስ ከተቋቋመበት 2011 ዓ.ም. አንሥቶ አንድ ሀገራዊ ምርጫ እና ሦስት ሕዝብ ውሣኔዎችን ማስፈጸሙ ይታወቃል።  ቦርዱ በቀጣይም የ7ኛውን ዙር ሀገራዊ ምርጫ ለማከናወን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል። 

ስለሆነም ቦርዱ በቀጣይ የሚያከናውናቸው ምርጫዎች ከዚህ በፊት ከተካሄዱት ምርጫዎች በአፈጻጸም ቀልጣፋና ጊዜው የሚጠይቀውን ዘመናዊነት የተከተሉ ለማድረግ፤  የምርጫ ጣቢያ እና የምርጫ ክልል ጽ/ቤቶች በተለያዩ ባለድርሻ አካላት በርቀታቸው፣ በመልካ-ምድራዊ አቀማጣቸው የታወቁ እና የተለዩ እንዲሁም ለመራጩ  ሕዝብ ምቹና ተደራሽ እንዲሆኑ፣

በተጨማሪም ሕግን መሠረት አድርገው የተቋቋሙ መሆናቸዉን የማረጋገጥ እና መረጃዎች በተሟላ መንገድ የማደራጀት ሥራ አስፈላጊ በመሆኑ፤ ምርጫ ጣቢያዎቹ የሚገኙበት ትክክለኛ ቦታዎች የGIS ቴክኖሎጂን በመጠቀም በ‘’XY Coordinate’’ የመለየት እና የመመዝገብ ሥራ እያከናወነ ይገኛል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ምንገድ ላይ

(በእውቀቱ ስዩም) በቀደም ከሆነ ቦታ ተነስቼ ወደ አልሆነ ቦታ ስራመድ...

ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ በጡረታ ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ...

አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ አዲስ መግለጫ አወጣች

ታዋቂዋ አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ ለስፖርት ወዳጆችና ለደጋፊዎቿ ወቅታዊ መረጃ...