የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ሳላህ በዚህ አመት ያሳለፈው ጊዜ ከምንጊዜውም የተለየ ነው ሲል ገልጿል።
ስለ ባሎን ዶር ሽልማት የተጠየቀው መሐመድ ሳላህ ” እንደዚህ አይነት አመት አሳልፌ አላውቅም በተለይ ከትልቅ ዋንጫ ጋር “ ሲል ተናግሯል።
ሳላህ አክሎም የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ካሸነፍኩ በኋላ “ ባሎን ዶር የማሸነፍ እድሌ ከፍ ያለ ይመስለኛል “ ብሏል።
የ እግርኳስ ፀሀፊዎች የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ የተመረጠው መሐመድ ሳላህ ሽልማቱን ትላንት ምሽት ተቀብሏል።
ለሽልማቱ ድምፅ ከሰጡ ጋዜጠኞች መካከል 90% ያህሉ መሐመድ ሳላህን መምረጣቸው ከዚህ በፊት መዘገቡ አይዘነጋም።
@Tikvahethsport
