ደጆችሽ አይዘጉ ማኅበር ከ130 በላይ አብያተ ክርስቲያናትን አስከፈተ

Date:

ደጆችሽ አይዘጉ ማኅበር ዋነኛ ዓላማው የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን አስከፍቶ አገልግሎት በማስጀመር ራሳቸውን እንዲችሉ ማድረግ ሲሆን አገልግሎቱን ለማከናወን በርካታ ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል።

አቶ ሙሉጌታ ተገኘ የደጆችሽ አይዘጉ ጠቅላላ ማኅበር የአዲስ አበባ ማዕከል ዋና ሥራ አስኪያጅ ማኅበሩ ከምሥረታው ጀምሮ በቁጥር ከ139 በላይ የሆኑ በሀገራችን የገጠር ክፍሎች የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን የማስከፈት ሥራዎች በመሥራቱ አገልግሎት ጀምረዋል ብለዋል፡፡

አክለውም ከማስከፈት ተግባራት በሻገር ከ54 ሺህ ብር በላይ በማውጣት ለተለያዩ አድባራት እና ገዳማት አገልጋዮች ወርኃዊ ደሞዝ ክፍያ መፈጸሙን እንዲሁም ለአብነት ትምህርት ማስኬጃ ከ19 ሺህ ብር በላይ ወጪ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በማኅበሩ የሐዋርያዊ ተልዕኮ ክፍል ኃላፊ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ወንድይፍራው በበኩላቸው በቅርቡ በ3 ወረዳዎች የአካባቢያቸውን ቋንቋ የሚችሉ፣በምእመናን እና በካህናት መካከል ያለውን የቋንቋ ችግር የሚፈቱ፣ባሉበት በቀዬአቸው የሚያገለግሉ የ60 ካህናት ሥልጠና እንደሚጀምር ገልጸዋል፡፡

አንድ የሆነው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እንዲሳካ በገቢ አቅማቸው የጎለበቱ በከተማ ያሉ አድባራት በገጠር  የሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትን በመደገፍ ረገድ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አቶ ቴዎድሮስ  አሳስበዋል፡፡

©ማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...