የከተማ አስተዳደሩ በበከሉ አማራጭ መፍትሄዎችን እየፈለገ መሆኑን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር ለመምህራን የመኖሪያ ቤት ለማቅረብ ያቀደው የ25/75 የቤት ልማት ፕሮጀክት በመምህራን ዘንድ ቅሬታን አስነሳ። መምህራን በኑሮ ጫና ምክንያት የቤቱን ዋጋ 25 በመቶ መቆጠብ እንደማይችሉ ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ መቆጠብ ለማይችሉ መምህራን የኪራይ ቤቶችን ለመገንባት ማቀዱን አስታውቋል።
በአዲስ አበባ ከተማ መምህራን ስብሰባ ላይ መምህራን እንደገለጹት፣ ዘጠኝ እና አስር አመት የስራ ልምድ ያለው መምህር የሚያገኘው 10 ሺህ ብር ገደማ ደመወዝ ለኑሮ በቂ ባለመሆኑ፣ ለቤት መሥሪያ የሚሆን 25 በመቶውን መቆጠብ ከባድ ነው።
