ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል የልብ ህክምና መሳሪያ ተበረከተ

Date:

ለኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል  በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነና ለበርካታ ህፃናት የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል የተባለ የልብ ህክምና መሳሪያ ተበረከተ::

የልብ ቀዶ ህክምናን ጨምሮ ሁሉንም የልብ ህክምናዎች በነፃ የሚሰጠው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል አገልግሎቶችን የሚሰጠው ከሚሰበስበው እርዳታ ከሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት በሚደረግለት ድጋፍ መሆኑን ተናግሯል፡፡

ማዕከሉ የህክምና መሣሪያ ድጋፉን ያገኘው ላይፍ ፎር አፍሪካ ከተባለ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን የልብ ህክምና መሳሪያው ለማዕከሉ የመጀመሪያ የሆነና ለበርካታ ህፃናትን በቀዶ ህክምና ጊዜ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የተደረገው የህክምና መሳሪያ ድጋፍ የልብ ቀዶ ህክምናው ከተከወነ በኋላ ልብ ሳይዘጋ ምን ያህል ለውጥ መጥቷል የሚለውን ለማየት የሚያግዝና ቀዶ ህክምናው ሳይጠናቀቅ ችግር ካለ ለመለየት የሚረዳ  በመሆኑ ተደጋጋሚ ቀዶ ህክምና እንዳይደረግና ስራውንም የሚጠይቀውንም ወጪንም የሚቆጥብ ነው ተብሏል፡፡

ላለፉት 7 ዓመታት ማህበራዊ ሚዲያ ለሰብዓዊነት በመጠቀም ማዕከሉን ስትረዳ በቆየችው በጎ አድራጊ ጋዜጠኛ ህይወት ታደሰ በተመሠረተው ላይፍ ፎር አፍሪካ  ተቋም የህክምና መሳሪያው መለገሱ ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል በኢትዮጵያ ብቸኛ የሆነና የነጻ የልብ ህክምና የሚሰጥ ማዕከል ሲሆን ማእከሉ ከመንግስት ምንም አይነት በጀት የማይመደበለትና ከተለያዩ ተቋማትና በጎ ፈቃደኞች በሚያገኘው ድጋፍ የሚንቀሳቀስ ነው ተብሏል፡፡

በተለይም ስራውን ለማስፋፋት በቂ የልብ ቀዶ ህክምና ባለሙያዎች ቢኖሩትም የግብዓት እጥረት ግን ትልቅ ፈተና እንደሆነበት ተነግሯ፡፡

በአሁኑ ሰአትም በማዕከሉ ከሰባት ሺ በላይ ሰዎች የልብ ህክምና ወረፋ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...