በህንድ ውቂያኖስ አካባቢ የሚገኘውና እንግሊዝ የጦር ቤዝ የሆነው ዲያጎ ጋርሺያ ካምፕ የኢራንን የኒኩለር ማበልጸጊያዎች ለመምታት ስትራቴጂክ ቦታ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የእንግሊዝ መንግስት ቦታውን ለመፍቀድ ማመንታቱ ተገልጹዋል፡፡
እንግሊዝና አሜሪካ ካላቸው ጥብቅ ወዳጅነት አንጻር ሙሉ ለሙሉ ለመከልከል ቢቸገርም ቦታውን ለአሜሪካ መፍቀድ ግን ብዙ ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮችን እንደሚያበላሽ ተገልጹዋል፡፡
የእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ስታርመር አሜሪካ ኢራንን የመምታት ፍላጎት አላት ወይ ተብለው ለተጠየቁት ሲመልሱ ምንም አይታወቅም ብለዋል፡፡
ሰውዬው ከዚህ በፊት ግን ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው አሜሪካ በጦርነቱ የመሳተፍ ፍላጎት እንደሌላት እርግጠና ነኝ ብለው ነበር፡፡
የእንግሊዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴቪድ ላሚም ከአሜሪካው አቻቸው ማርኮ ሩቢዮ ጋር አስቸኳይ ውይይት ለማድረግ ወደ ዋሽንግተን ተጉዘዋል።
የእንግሊዝ ባለስልጣናት አንዳንድ ልዩ ሁኔታዎች እስካልተፈጠሩ ድረስ ሃገሪቱ በኢራን ላይ በሚደረግ ማንኛውም ጥቃት ላይ እንደማትሳተፍ ገልጸዋል ሲል የዘገበው ዘጋርዲያን ነው፡፡
