የታዋቂው ቢሊየነር የኢሎን መስክ ንብረት በሆነው ስፔስ ኤክስ ወደ ጠፈር ሊመጥቅ የተዘጋጀው የዓለማችን ትልቁ ሮኬት በሙከራ ላይ እያለ መፈንዳቱ ታውቋል።
ትናንት ምሽት በደቡባዊ ቴክሳስ በሚገኘው የሮኬት ጣቢያ ሊመጥቅ ሲል በመሬት ላይ እያለ ፍንዳታ ያጋጠመው ስታርሺፕ 36 ሮኬት በዓለማችን እስከዛሬ ከተገነቡት ሁሉ ግዙፉ መሆኑን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
አጠቃላይ ቁመቱ የባለ 40 ወለሎች ፎቅ ያህል ወይም 120 ሜትር እንደሚረዝምም ነው የተነገረው።
ዝግጅቱ በርካታ ወራትን የፈጀው እና 90 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተደረገበት ስታርሺፕ 36፣ ትናንት በሙከራ ላይ እያለ በፈነዳበት ወቅት በሰው ሕይወት ላይ ያጋጠመ ምንም አይነት ጉዳት እንደሌለ ተገልጿል።
