በፈረንጆቹ 2035 የሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፉ ለአፍሪካ የጥቅል ምርት(GDP) 1 ትሪሊየን ዶላር ሊጨምር እንደሚችል የአህጉሪቱ የልማት ባንክ ገልጿል።
አካታች ከሆነ ዘርፉ በ2035 ከ35-40 ሚሊየን ስራዎችንም ሊፈጥር እንደሚችል ባንኩ ሲገልጽ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ የአፍሪካን አሁናዊ ኢኮኖሚ አንድ ሶስተኛ ነው ተብሏል።
ይህንን ለማሳካት አህጉሪቱ 6 የመረጃ ማዕከላትን ጨምሮ እስከ 3 ሚሊየን በዘርፉ የሰለጠኑ ባለሙያዎች ያስፈልጋታል ተብሏል።
ከAI ከሚገኘው ጥቅም 58 በመቶ ወይም 580 ቢሊየን ዶላር ያህሉን 5 ዘርፎች እንደሚያገኙ ሲጠበቅ ግብርና በ20% ቀዳሚው ነው።
በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተካሔደ ውይይት ላይ ኢትዮጵያ የAI ዩኒቨርሲቲውን ለመገንባት የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በሚቀጥሉት 6 ወራት ውስጥ እንደሚጠናቀቁ መግለጻቸው ይታወሳል።
ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ብቃት ያላቸውን ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ለ100 ተማሪዎች ኮታ እንዲሁም ከኢትዮጵያ ሁለት በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች በከፍተኛ ውድድር ተመርጠው እንደሚገቡ ጠቁመዋል፡፡
በተመሳሳይ ሰሜን አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሮኮ የAI ዘርፉ በ2030 ሃገራዊ ጥቅም ምርቷ ላይ 10 ቢሊየን ዶላር እንደሚጨምርና እስከ 50ሺህ ስራዎችን እንደሚፈጥር ገልፃ በዘርፉ እስከ 200,000 ሰዎችን ለማሰልጠን ማቀዷንም ገልፃለች።
ዘገባው የሮይተርስና የEcofin ኤጀንሲ ነው።
|@tikvaheth magazine
