ለመጀመሪያ ጊዜ የሶስት ሰዎች ዲ ኤን ኤ (DNA) የተወለደው ህጻን ሙሉ ጤንነት ላይ ነው

Date:

በአለም የህክምና ታሪክ ታላቅ ስኬት ተብሎ የተመዘገበውና የሶስት ሰዎችን የዘር ማንነት (DNA) በመጠቀም የተወለደው የመጀመሪያው ህጻን፣ አደገኛውንና ገዳዩን የዘር ውርስ በሽታ በማሸነፍ ሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተረጋግጧል።
 
የህጻኑ እናት ከዚህ ቀደም የሁለት ልጆቿን ህይወት የቀጠፈውንና በነርቭ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርሰውን ‘Leigh syndrome’ የተሰኘ አደገኛ የዘር ውርስ በሽታ ተሸካሚ ነበሩ። ይህንን በከፍተኛ ሁኔታ የሚተላለፍ ገዳይ በሽታ ለመከላከል የህክምና ባለሙያዎች ‘Mitochondrial replacement’ የተሰኘውን እጅግ ዘመናዊና ፈር ቀዳጅ የህክምና ጥበብ ተጠቅመዋል።
 
በዚህም መሰረት ህጻኑ 99.9 በመቶ የሚሆነውን ዋነኛ የዘር ማንነቱን (Nuclear DNA) ከእውነተኛ ወላጆቹ የወሰደ ሲሆን፣ በሽታውን ለመከላከል የሚያስችለውን እጅግ አነስተኛና ጤናማ ‘Mitochondrial DNA’ ደግሞ ከአንዲት በጎ ፈቃደኛ ሴት አግኝቷል።
 
ይህ ከለጋሿ የተገኘው የዘር ፍሬ የህጻኑን መልክ፣ ስብዕናም ሆነ ሌሎች ተፈጥሯዊ ማንነቶች በፍጹም የማይቀይር ሲሆን፣ ብቸኛ ስራው ጤናማ ሴሎችን በመገንባት አስከፊውን የዘር ውርስ በሽታ መከላከል ብቻ ነው።
 
ይህ በስኬት የተጠናቀቀው አስደናቂ የህክምና ታሪክ፣ በተመሳሳይ የዘር ውርስ በሽታ ለሚሰቃዩ በርካታ ቤተሰቦች ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ ሲሆን፤ ከዚያ በኋላ ባሉት ዓመታትም በርካታ ህጻናት በተመሳሳይ የህክምና ዘዴ ከበሽታው ነጻ ሆነው በጤና እንዲወለዱ በር ከፍቷል።
 
አንዳንዴ እጅግ ጥቃቅን የምትባለው የዲ ኤን ኤ (DNA) ክፍል የአንድን ሙሉ ቤተሰብ የወደፊት እጣ ፈንታ የመቀየር ትልቅ አቅም አላት ነው የተባለው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ12ኛ ክፍል ተፈታኞች  565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ አላሳለፉም

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በተመዘገበው ውጤት...

የአማርኛ ቋንቋ እውነተኛ ምንጭ ቤተ መንግሥት ሳይሆን ሕዝብና ሠራዊት ነው

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአማርኛ ቋንቋ ማበልጸጊያ ተቋም አዘጋጅነት ከስድስት...

አዲስ አበባ፦ የዜጎች ቀይ መስመር!

(የግል አስተያየት) አዲስ አበባ የኢትዮጵያውያን መናገሻ፣ የበርካታ ብሔረሰቦች ባህሎች ለዘመናት...

አብን የምክክሩን ውጤት ውድቅ አደረገ!

አብን በሀገራዊ ምክክሩ ማጠቃለያ ላይ የተፈጸመውን “ሕገ-ወጥ ጣልቃ-ገብነት” በመቃወም...