በጤና ተቋማት ላይ በየአመቱ በሚደረግ ቁጥጥር ብዙ ግኝቶች መኖራቸውን የገለፁት በጤና ሚኒስቴር የጤናና ጤና ነክ ተቋማትና ባለሙያዎች ቁጥጥር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ እንዳልካቸው ፀዳል ናቸው።
ከእነዚህም ውስጥ አንደኛውም በመንግስት በጀት ተገዝተውና ለማህበረሰቡ በነፃ የሚሰጡ መድሀኒቶችን ከመንግስት ተቀማት ወጥተው ሲሸጡ መገኘታቸውን እንደሆነም ተናግረዋል።
እነዚህ ተቋማት ላይም አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አንስተው በተመሳሳይም በመደበኛ አሰራር ለታካሚዎች የሚውሉ መድሀኒቶች በህገወጥ መንገድ እንደሚወጡም ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በቁጥጥር ወቅት በየደረጃው በቂ የሆነ እውቀትና ችሎታ እንዲሁም የህክምና መሳሪያ ሳይኖር ነገር ግን ከአቅም በላይ የሚሰሩ ተቋማት መገኘታቸውን አንስተዋል፡፡
የንፅህና አያያዝ ስርዓቱ ላይም ከፍተኛ ችግር የታየባቸው መገኘታቸውን አንስተው ይህም በአጠቃላይ የታካሚ ደህንነት ችግር ውስጥ መሆኑን ጠቁመዋል።
በመሆኑም አጠቃላይ በመድሀኒት አቅርቦትና ዙሪያ ያለውን ችግር ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሚሰራው ስራ በስፋት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ስራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል።
አሐዱ ራድዮ
