ለተማሪዎች ቪዛ መስጠት የጀመረችው አሜሪካ የአመልካችን የማህበራዊ ሚዲያ ልትፈትሽ ነው

Date:

አሜሪካ ከዚህ ቀደም ለተማሪዎች ቪዛ ለመስጠት የጀመረችውን የአመልካቾችን የማህበራዊ ሚዲያ መፈተሽ ወደ H-1B ቪዛ ልታሰፋ ነው።

የትልልቀ ክህሎት እና ሙያ ባለቤቶች ወደ አሜሪካ ለስራ ሲያቀኑ የሚሰጣቸው የH-1B ቪዛ ከዚህ በኋላ ሲሰጥ የማህበራዊ ሚዲያቸው እንደሚታይ ተገልጿል።

የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት የዚህ ቪዛ አመልካቾች የማህበራዊ ሚዲያቸውን ወደ “public” እንዲቀይሩ ያዘዘ ሲሆን የአሜሪካን ብሄራዊ ጥቅም የሚጎዳ ተግባር እንዳልፈፀሙ ይታያል ብሏል።

የH-1B ቪዛ የአሜሪካ ተቋማት በተለይ በህክምና፣ ቴክኖሎጂ እና ፋይናንስ ላይ ልዩ ችሎታ ያላቸውን የውጪ ሃገራት ዜጎች እንዲቀጥሩ የሚፈቅድላቸው ሲሆን ከማህበራዊ ሚዲያ ፍተሻው በተጨማሪ አመልካቾች በኦንላይን ደህንነት፣ በሃቅ ማጣራት፣ በመረጃ ማዛባት፣ በይዘት ቁጥጥር እና ሌሎችም ተያያዥ ስራዎች ላይ ስለመሰራታቸውም ይታያል ተብሏል።

አሜሪካ ከዚህ በፊት በተራድኦ ድርጅቷ በኩል የሚደረጉ የመረጃ መዛባትን  መከላከልና የሃቅ ማጥራት ስራዎችን ትደግፍ እንደነበር ሲታወስ አሁን ላይ ግለሰቦቹ በነዚህ ዘርፎች መስራታቸው ቪዛ ለመሰጠት መታየቱ ግርምትን አጭሯል።

አሜሪካ በአንድ ወቅት ትደግፋቸው የነበሩትን እነዚህ ተግባራት ሃሳብን በነፃነት መግለፅን የሚገድቡ የሳንሱር ተግባር እንደሆኑ ማስረጃ ካለ አመልካቾች ቪዛ ይከለከላሉ ብላለች።

የትራምፕ አስተዳደር እነዚህን ተግባራት ከሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ተፃራሪ አድርጎ የሚመለከታቸው ሲሆን ትራምፕ ወደ ቢሮ ከተመለሱ በኋላ የፌደራል ሳንሱርን ማገዳቸው ሲታወስ፣ የውጪ ጉዳይ ቢሮውም የማህበራዊ ሚዲያ ይዘቶች ላይ ቁጥጥር እንዲደረግ ጫና የሚያደርጉ የውጪ ዜጎች ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እንደሚያደርግ መግለፁ ይታወሳል።

ዘገባው የአልጄዚራ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...