በመላ ሰሜን አሜሪካና በሌሎችም የዓለማችን አገራት የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ የከበረ ጥልቅ ሰላምታዬን አቀርባለሁ።
እንደምታውቁት ከሁለት ኢትዮጵያውያን የተወለደችው ሀበሻዊቷ ግን በዜግነት አሜሪካዊት የሆነችው ለአሜሪካ የኮንግረስ አባልነት እየተወዳደረች ትገኛለች።
በታሪክ እስከዛሬ እንዳየነው ( ያውም በእሷ ዕድሜ) ለአሜሪካ ኮንግረስ ለመመረጥ የሞከረ ኢትዮጵያዊ የለም ።
ሜላት ይህንን ያልተሞከረ ነገር አሸንፋለሁ ብላ በፅናት መጀመሯ ከልብ የምታኮራ ጀግና የኢትዮጵያውያን ልጅ መሆኗን በተግባር አስመስክራለች።
በዚህ የዓለማችን ትልቅ የፖለቲካ መድረክ ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን ግዳጇን ተወጥታለች።
አሁን ቀሪው ስራ የኛ በዓለም ዙሪያ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ይሆናል ማለት ነው።
የሜላት በዚህ የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ በሆነው ኮንግረስ ውስጥ መግባት እንደ አገር ለኢትዮጵያ እንደ ዜጋ ለኢትዮጵያውያን ከሚሰጠው ቀላል ያልሆነ ጥቅም ባሻገር ወደር የሌለው ኩራትና ክብር ያጎናፅፈናል።
በመሆኑም የሜላት ማሸነፍ የሁሉም ኢትዮጵያዊ አሽናፊነት መሆኑ በፍፁም አያጠራጥርም።
ሜላት ውድድሩን አሸንፋ ለውጤት እንድትበቃ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ድጋፍና አስተዋፅኦ ወሳኝ ነው።
በውድድሩ አሸንፎ ለመውጣት ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ የፋይናንስ አቅም በመሆኑ በዚህ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያን ሁሉ አንድ ሆነን በአንድ ልብ ተነስተን እንደየአቅማችን በማዋጣት በሜላት አማካኝነት ኢትዮጵያ አገራችንን በዓለም መድረክ እናስጠራት።
በመላ ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ተሳታፊዎች እና ተፅእኖ ፈጣሪዎች ሙሉ ትኩረታችሁን የሜላት ምርጫ ላይ በማድረግ እጅ ለእጅ ተያይዘን ኢትዮጵያን ወደ አሜሪካ ኮንግረስ እናስገባት።
በሜላት የኮንግረስ ወንበር አገራችን እንደ ኮከብ ደምቃ፣ እንደ ፀሐይ ፈክታ ለማየት በሙሉ ልብ እነሳ።
ሜላት ጀግናችን ናት!!!
ሜላት ኩራታችን ናት!!!
ሜላት የአገራችን ክብር ናት!!!
ሜላት ታሸንፋለች !!!
አመሰግናለሁ.
ጋዜጠኛ ሰሎሞን አስመላሽ
