ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር ተሾመለት

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር ሆነው ለተሾሙት አቶ ባረክ ታደሰ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ የእንኳን ደህና መጡ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የኢትዮጵያውያን ቤት እንድሆን እንሰራለን፤ የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር የተሻለ ውጤት እንድመዘገብ የአሰራር መመሪያዎችንና ደንቦችን ተከትሎ የሚተገብርና የሚያስተገብር አመራር መኖር ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ዘርፉን ወደ ተፈለገው ደረጃ ከፍ ለማድረግም ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ባረክ ታደሰ ትልቅ አቅም በመሆናቸው እንኳን ደህና መጡ ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት አቶ ባረክ ታደሰ በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል ልባዊ ምስጋና በማቅረብ ሀገራችን በኪነጥበቡ ዘርፍ ተጠቃሚ እንድትሆን ሁሉን ያማከለ ኪናዊ ስራዎችን ከታችኛው አደረጃጀት ጀምሮ በጋራ መስራትን ይጠይቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የተሰጠኝን ሃላፊነት በአግባቡ ለመወጣትም አቅጣጫ ሰጭ ከፍተኛ አመራሮች ከጉኔ በመኖራቸው እድለኛ ነኝ ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...