ለኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢዎች እስከ 250 ሺህ ዶላር ዋስትና

Date:

የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ለመሰማራት በሚፈልጉ የኤሌክትሮኒክስ ደረሰኝ ሶፍትዌር አቅራቢዎች ላይ እንደ የደረጃቸው እስከ 250,000 የአሜሪካ ዶላር የሚደርስ የፋይናንስ ዋስትና የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።

በዚህ ወር አጋማሽ ላይ የወጣው መመሪያ በሀገሪቱ የታክስ ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውስጥ የገበያ መግቢያ አዲስና ፈታኝ መስፈርት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የዋስትናው መጠንም በአቅራቢው የአገልግሎት ዓይነትና በሚያገለግሉት ግብር ከፋዮች ልኬት ላይ ተመስርቶ በ10 ደረጃዎች የተከፋፈለ ነው።

በዚህም መሰረት የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አቅራቢዎች 30,000 ዶላር፣ የሶፍትዌር-አስ-አ-ሰርቪስ አቅራቢዎች 50,000 ዶላር፣ የኢ-ኮሜርስና ዲጂታል ገበያ አንቀሳቃሾች 25,000 ዶላር፣ እንዲሁም የራሳቸውን የውስጥ ደረሰኝ ሥርዓት የሚጠቀሙ ግብር ከፋዮች 15,000 ዶላር የባንክ ወይም የኢንሹራንስ ዋስትና ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

የዋስትናው መጠንም አቅራቢዎች የሚያገለግሏቸው ደንበኞች ቁጥር ወይም የሽያጭ ልውውጣቸው እያደገ ሲሄድ በየሁለት ዓመቱ የሚታደስ ሲሆን፣ ከ40 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮችን ለሚያገለግሉ ወይም ከ1 ትሪሊዮን ብር በላይ ዓመታዊ ሽያጭ ላላቸው ድርጅቶች ከፍተኛው የዋስትና ጣሪያ 250,000 ዶላር ይደርሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ከፖለቲካ ራሳቸውን አገለሉ

ላለፉት 5 አስቸጋሪና ፈታኝ ዓመታት (ከ2014 እስከ 2018 ዓ.ም)...

ንባብ ለሕይወት  እየመጣ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

“ወጣቱን በጉልበት እያፈሱ ወደ ጦርነት እየነዱት ነው!”

"ሰላም፣ ዴሞክራሲና ልማት በትግራይ፦ የመገናኛ ብዙኃን እና የማኅበረሰብ አንቂዎች...