” ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናውን ሲጨርስ Finish and Submit ሳያደርግ መውጣት የለበትም “

Date:

አጠቃላይ 190 ሺህ ተፈታኞች ፈተናቸውን በኦንላይን ይወስዳሉ።

የመጀመሪያ ቀን የኦንላይን ፈተና ውሎን ተከትሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

በዚህም ፤ ” ማንኛውም ተፈታኝ ፈተናውን ሲጨርስ Finish and Submit ሳያደርግ መውጣት የለበትም ” ብሏል።

” ተፈታኙ ይህንን ማድረጉንም በፈተና ክፍሉ የተመደበ ባለሙያ ማረጋገጫ ሳይሰጠው እና ተፈታኙም ፈተናውን መጨረሱን በፊርማው ሳያረጋግጥ ከመፈተኛ ክፍል መውጣት አይኖርበትም ” ሲል አሳስቧል።

ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል እንደገቡ ማሳወቅ እና ለዚህ ጉዳይ ተባባሪ ሆኖ ካልተገኙም በፈተና ማስፈጸሚያ ፕሮቶኮል መሰረት ተገቢው የእርምት ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ አዟል።

ሌላው ሚኒስቴሩ ፥ በተለያየ ምክንያት ” ሲስተም ዘጋብን ” በማለት ፈተና ክፍል ውስጥ የሚቀመጡ ተፈታኞችን በተለያዩ መንገዶች የማጣራት ሥራ በመስራት አስፈለጊውን የእርምት ወይም አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰድ እንደሚኖርበትም አሳስቧል።

ለምሳሌ፦ ስንተኛ ጥያቄ ላይ እንዳለ ወይም እንደዘጋበት / ባት መጠየቅ እና የተሰጠው መልስ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣረስ ሆኖ ከተገኘ በፈተና ማስፈጸሚያ ፕሮቶኮል መሰረት ተገቢውን እርምጃ እንዲወሰድ ብሏል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...