ሳይታገቱ ታግተናል ያሉት ህፃናት

Date:

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው ኳስ ሜዳ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ነው።

አጋችና ታጋች በመምሰል የማታለል ወንጀሉን የፈፀሙት አራቱ ተጠርጣሪዎች ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ሁለት ወንዶችና ሁለት ሴቶች ሲሆኑ ለሁለት ቀናት ከቤተሰቦቻቸው ወጥተው ሲዝናኑ ቆይተው ገንዘብ ሲያጥራቸው በመመካከር ለቤተሰብ ስልክ ደውለዋል፡፡

ወንዶቹ አጋች ሴቶቹ ደግሞ ታጋቾች በመሆን ለሴቶቹ ቤተሰቦች በደወሉት ስልክ 5 መቶ ሺ ብር የጠየቁ ሲሆን የሴት ወላጆች አቅራቢያቸው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ቀርበው ጥቆማ ሠጥተዋል።

ፖሊስም ለቀረበው ጥቆማ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት መረጃዎችን በማሰባሰብ አራቱንም ተጠርጣሪዎች ካሉበት ቦታ በቁጥጥር ስር ሊያውላቸው ችሏል፡፡

የታዳጊዎቹ ቤተሰቦች በወቅቱ ሴት ልጆቻቸው መታገታቸውን ሲሰሙ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገብተው እንደነበር ተናግረው ፖሊስ ላከናወነው ተግባርም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በልጆች አስተዳደግ ዙርያ የቤተሰብ ኃላፊነት ከፍተኛ ሲሆን በአንዳንድ ታዳጊ ወጣቶች ላይ የሚስተዋለው ባህሪ የነገ ተስፋቸውን ሊያጨልም የሚችል በመሆኑ ሊታረምና በወላጆች ዘንድም ከፍተኛ ጥንቃቄና ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን ያቀርባል ።
*

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የተፈናቀሉ ዜጎች በተጠለሉበት አካባቢ በቋሚነት መኖር የሚያስችላቸው 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን የዳሰነች ወረዳ ከበኦሞ...

ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ 11ኛውን የኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት በደብረ ብርሃን ከተማ አስመረቀ

ታዋቂው አትሌትና ባለሀብት ሻለቃ ኃይሌ ገብረሥላሴ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ...

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተዘጋጀው የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል ስቴት ኤግዘቢሽን ተከፈተ

በኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር አዘጋጅነት የመጀመሪያው አህጉራዊ የሪል...

በሊባኖስ እና በእሰራኤል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ተራዘመ

ትራምፕ በሊባኖስ እና በእሰራኤል መካከል የተደረሰው የተኩስ አቁም በሦስት...