የአሜሪካ ፍትሕ መስሪያ ቤት፣ ቦይንግ በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ከተከሰከሱት ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ጋር በተያያዘ “የማጭበርበር ወንጀል” ክሱን ላለመመስረት ከኩባንያው ጋር ከስምምነት መድረሱን ሮይተርስ ዘግቧል።
በስምምነቱ መሠረት፣ ቦይንግ በአውሮፕላኖቹ አመራረት ጥራት ላይ በውጭ ተቆጣጣሪ አካል የሚደረግበት ቁጥጥር እንደሚቀርለት ዘገባው ጠቅሷል። የተጎጂዎች ቤተሰቦች ጠበቆችና ሁለት የአሜሪካ ሴናተሮች፣ ክስ እንዳይቀር ጠይቀው ነበር።
ፍርድ ቤት፣ በሰኔ ወር ክሱን ለማየት ቀጠሮ ይዞ የነበረ ሲኾን፣ ቦይንግም “በማጭበርበር” ወንጀል ጥፈተኝነቱን እንደሚያምን ገልጦ ነበር። ከ1 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር በላይ በቅጣትና ለተጎጂዎች በካሳ ይከፍላል።
ዋዜማ
