ስኬት ባንክ አ.ማ የባለአክስዮኖች 3ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን ህዳር 20 ቀን 2018 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል አካሂዷል፡፡
በጉባኤው ላይ የስኬት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ጥላሁን ወርቁ የ2024/2025 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች ያቀረቡ ሲሆን ባንኩ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት አጠቃላይ የካፒታል መጠኑ 9.4 ቢሊዮን ብር መድረሱን እንዲሁም 1.24 ቢሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማስመዝገቡንም ተናግረዋል።
ባንኩ በ2024/25 በጀት ዓመት ጠቅላላ የሃብት መጠኑን 19.3 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን የተከፈለ የካፒታል መጠኑን ከ6.9 ቢሊዮን ብር ወደ 7.84 ቢሊዮን ብር ያሳደገ ሲሆን ጠቅላላ የደንበኞቹን ቁጥር 615 ሺህ ማድረስ መቻሉን በጉባዔው ላይ ተገልጿል፡፡
