ስዋዲናዊዉ አጥቂ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል!

Date:

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሀያ ሰባተኛ ሳምንት ጨዋታ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች በመባል የአርሰናሉ አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ መመረጡ ይፋ ተደርጓል። በዚህም መሰረት የአርሰናሉ የፊት መስመር አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል

የ 27 አመቱ የመድፈኞቹ አጥቂ ቪክቶር ዮኬሬሽ በለንደን ደርቢ ጨዋታ አርሰናል ቶተንሀምን ባሸነፈበት ጨዋታ ሁለት ምርጥ ጎሎችን ማስቆጠሩን ተከትሎ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምርጥ ተጫዋች ተብሎ በይፋ ተመርጧል።

የቀድሞ የአርሰናል ተጫዋች የነበረዉ ኢያን ራይት “ቪክቶር አሁን ከቡደኑ ወሳኝ ተጫዋች ዉስጥ አንዱ ለመሆን ሁሉም ነገር አለዉ በጥሩ ሰአት ወደ ብቃቱ መመለሱ ለአርቴታ ደስታን የሚፈጥር ነዉ” ሲል ራይት አስተያየቱን ሰቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የሚያደርጉት ድርድር እስኪጠናቀቅ ድረስ የተኩስ አቁሙ መራዘሙን አስታወቁ

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፓኪስታን ጥያቄ መሠረት ከኢራን ጋር የገቡትንየተኩስ...

ለኢትዮጵያ የግብርና ዘርፍ የሚውል የ40 ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ተፈቀደ

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ የልማት ክንፍ የሆነው ኢአይቢ ግሎባል (EIB...

ሃይንከን በአልኮል መጠኑ ጠንከር ያለ ቢራ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋወቀ

ሃይንከን ኢትዮጵያ በእለም አቀፍ ደረጃ ዝነኛ የሆነውን ዴሰፔራዶስ (Desperados)...