ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የ23ኛው የዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን ሆናለች፡፡
በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ በዛሬው ዕለት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ስፔንና አርጀንቲና የመደበኛ ጨዋታ ክፍለ ጊዜውን ያለምንም ግብ አቻ በማጠናቀቃቸው ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ አምርተዋል፡፡
በተጨማሪ ደቂቃውም ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ የ2026ቱን የዓለም ዋንጫ ማንሳት ችላለች፡፡
የስፔንን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፌራን ቶሬስ ከመረብ ያሳረፈ ሲሆን ÷ በዚህም ስፔን በታሪኳ ለ2ኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማሳካት ችላለች፡፡
