የኢራን ጠቅላይ መሪ አገራቸው ለአሜሪካ “የማይረሳ ትምህርት” ማዘጋጀቷን ተናገሩ

Date:

  1. የኢራን ጠቅላይ መሪ ሞጅታባ ኻሜኒ፤ አሜሪካ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነቱን “በተደጋጋሚ መጣሷ” የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ፊርማ ዋጋ የለሽ እንደሆነ” የሚያሳይ ነው አሉ።
  2. በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት የተገደሉትን አባታቸውን ተክተው ሥልጣኑን ከተቆጣጠሩ አንስቶ እስካሁን በይፋ ያልታዩት ጠቅላይ መሪው ይህንን ያሉት በጽሑፍ ባወጡት መግለጫ ነው።
  3. አሜሪካ “ግጭቱን ለማባባስ” ትፈልጋለች በማለት የከሰሱት ሞጅታባ ኻሜኒ፤ ኢራንም ለዋሽንግተን “የማይረሳ ትምህርት እንዳዘጋጀችላት” ገልጸዋል።
  4. አሜሪካ እና ኢራን ጦርነቱን የሚቋጭ የመጨረሻ ድርድር እንዲያደርጉ በር የሚከፍት የመግባቢያ ስምምነት የተፈራረሙት ሰኔ ላይ ነበር።
  5. በአሜሪካ በኩል የፈረሙት ፕሬዝዳንት ትራምፕ ሲሆኑ፤ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ደግሞ ኢራንን ወክለው ፊርማቸውን አኑረዋል።ይሁን እንጂ በሳምንታት ልዩነት የሁለቱ አገራት ግጭት አገርሽቷል።
  6. ፕሬዝዳንት ትራምፕም ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጊዜያዊው ስምምነት “አብቅቷል” ብለዋል።አሜሪካ ስምምነቱን “በተደጋጋሚ መጣሷን” በማንሳት የከሰሱት የኢራኑ ጠቅላይ መሪ፤ ይህም “አንድ መሠረታዊ እውነት አሳይቷል፤ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ፊርማ ሙሉ በሙሉ ዋጋ የለሽ እና ተዓማኒነት የጎደለው ነው” ብለዋል።
  7. “አሁን የአሜሪካ ጠላት ግጭቱን ለማባባስ እየፈለገ ነው፤ ለዚህም ከፍተኛ ዋጋ እና ተጨማሪ ውርደት ያጋጥመዋል። የተከበረችው አገር ኢራን እና የሪዚስታንስ ግንባር የማይረሳ ትምህርት እንዳዘጋጁለት ሊያውቅ ይገባል” ሲሉም በቴሌቪዥን በተነበበው መግለጫ አስጠንቅቀዋል።
  8. BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ጄኤፍኤም 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ለ6 ወራት ታገደ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባደረገው የይዘት ክትትልና የኢንስፔክሽን ምልከታ...

ሱልጣን ቢን ኻሊፋ ግሩፕ በኢትዮጵያ በሆቴል ዘርፍ ሊሰማራ ነው

በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የኢፌዲሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር...

የአሜሪካ የታክስ ህግ የስፔንን የዓለም ዋንጫ ሽልማት ስጋት ላይ ጣለ

የስፔን ብሔራዊ ቡድን ከዓለም ዋንጫ ሊያገኘው ከሚችለው 50 ሚሊዮን...

ህወሓት ከሌሎች ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር የሚደረግ ጥምረት አስፈላጊ መሆኑን ገለጸ

ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ...