በአለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ስፔን ከቤልጂየም ያደረገችውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችላለች።
የስፔንን የድል ግቦች ሚኬል ሜሪኖ እና ፋብያን ሩይስ ሲያስቆጥሩ ለቤልጂየም ዲ ኪትሌይር ከመረብ አሳርፏል።
ሚኬል ሜሪኖ በተከታታይ ጨዋታዎች ተቀይሮ ገብቶ የስፔንን የማሸነፊያ ወሳኝ ግብ አስቆጥሯል።
ስፔን በግማሽ ፍፃሜው ከፈረንሳይ ጋር ማክሰኞ ምሽት 4:00 ሰዓት በቴክሳስ ዳላስ ስታዲየም ትገጥማለች።
