በ10 ዓመቱ 450 መጽሐፍትን ያነበበው “መጽሐፍት አዳኙ” ታዳጊ አሜን!

Date:

​”ጓደኞቹ በጌም ሲጠመዱ፤ እሱ ግን የዕውቀት ባህር ውስጥ ይዋኛል”

​በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ብዙ ታዳጊዎች ስልክ ላይ አቀርቅረው ማየት የተለመደ ቢሆንም፤ የ10 ዓመቱ አሜን ባሳዝነው ግን የተለየ መንገድ መርጧል። የምስካዬ ኅዙናን መድሃኒዓለም ትምህርት ቤት የ5ኛ ክፍል ተማሪው አሜን፤ በዚህ በለጋ እድሜው ከ450 በላይ መጽሐፍትን በማንበብ ብዙዎችን አስደምሟል።

​የአሜን ስኬት ምስጢር ምንድን ነው?

እናቱ መምህርት እሴተ ታዬ እንደሚሉት፤ አሜን ገና በእርግዝና እያለ ጀምሮ ይነበብለት ነበር። በቤታቸውም “የቤተሰብ ንባብ” ፕሮግራም ስላለ፤ ሁሉም በአንድነት መጽሐፍ ያነባሉ።

​አሜን ምን ይላል?

“የሰው ልጅ ከቴክኖሎጂ በላይ እውቀትን ማግኘት የሚቻለው በመጽሐፍ ነው። ንባብ በትምህርቴ ጎበዝ እንድሆን ብቻ ሳይሆን፣ ችግሮች ሲያጋጥሙኝ መፍትሄ እንድፈልግም አግዞኛል” ይላል።

​ከአንባቢነት ወደ ደራሲነት:
ይህ ብሩህ ታዳጊ አሁን የራሱን መጽሐፍ እያዘጋጀ ነው። “ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰዎች ለኢትዮጵያ ልጆች” የተሰኘው መጽሐፉ በመጪው የካቲት 11 (በልደቱ ዕለት) ይመረቃል ተብሎ ይጠበቃል።

​”ልጆች ‘አንብቡ’ የሚለውን ቃል ከመስማት ይልቅ፣ ቤተሰቦቻቸው ሲያነቡ ማየትን ይመርጣሉ” – መምህርት እሴተ ታዬ (የአሜን እናት)

​አሜንን እንኳን ደስ አለህ እያልን፤ ወላጆች ይህንን ልምድ ከቤታችን ብንጀምርስ?

​ሚካኤል ህሩይ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ እና ኢራን ዳግም ወደ ድርድር ?

ኢራን ከአሜሪካ ጋር በሚደረገው ድርድር ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣች፣ ነገር...

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት የሐማስ ከፍተኛ የደኅንነት ባለሥልጣን መገደሉ ተዘገበ

እስራኤል እሁድ ዕለት በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት በሐማስ የሚመራው የፍልስጤም...

አሰቃቂውን ጥቃት የፈጸሙ ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ ፓትርያርኩ ጠየቁ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፣ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት...

በአዲስ አበባ ጉዳይ የገዢው ፓርቲ አባላት ለሁለት ተከፍለዋል

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በ11ኛ ቀን ውሎው በ”ንዑስ” ቡድን...