የኢትዮጰያ ደም እና ህዋስ ባንክ አገልግሎት በ2017 በጀት ዓመት ውስጥ የአይን ብሌን ተከላ እና ቃል የማስገባት ስራዎች መስራቱን አስታውቋል፡፡
በዚህም የክረምቱ መርዓ ግብር ላይ ባሳለፍነው ሐምሌ ወር 100 ሰዎች የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የገቡ ሲሆን 58 የዓይን ብሌን ለመሰብሰብ ችለናል ሲሉ የኢትዮጰያ ደም እና ህዋስ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ የዓይን ብሌን መሰብሰብ እንደተቻለ እና የዓይን ብሌናቸውን ለመለገስ ቃል የሚገቡ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገልፆል፡፡
በኢትዮጰያ የዓይን ባንክ አገልግሎት በአዲስ አበባ ብቻ ይሰጥ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በጅማ ሪፈራል ሆስፒታል በቀጣይ ዓመት መጀመሪያ ወር ጀምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥ እና ባለሙያዎችም ሰልጠጥነው ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡ ነው
የዓይን ብሌን የማሰባብሰብ ስራ ሲሰራ የኤችአይቪ ፣ኮቪድ፣ የጉበት ቫይረስ እና ሌሎች በሽታዎች ቅድመ ምርመራ ይከናወናል፡፡በኢትዮጰያ በዓይን ብሌን ጠባሳ ምክንያት ብርሃናቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከፍተኛ በመሆኑ የዓይን ብሌን ልገሳ ለማድረግ የእድሜ ገደብ የሌለው በመሆኑ ህብረተሰቡ ቃል ሊገባ ይገባል ሲሉ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
