የአዲስአበባ መንገዶች ባለስልጣን በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በተሽከርካሪዎች ግጭት ሳቢያ ከ 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት መድረሱን አስታወቀ
ባለስልጣኑ ከጉዳት አድራሾችና ከሌሎች የመንገድ ጉዳት ካሣ ክፍያዎች ከ23 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ ሰብስቧል ተብሏል።
ባለፉት 9 ወራት በአጠቃላይ 182 የግጭት አደጋዎች የደረሱ መሆኑን ተቋሙ ገልፆል።
51 የሚሆኑት በቀለበት መንገድ ላይ የተከሰቱ ሲሆን፣ 131 የግጭት አደጋዎች ደግሞ ከቀለበት መንገድ ውጪ ባለው የከተማዋ መንገዶች ላይ የደረሰ ጉዳት መሆኑን አስታዉቋል።
በእግረኛ መንገዶች ላይ የግንባታ ግብዓትና ተረፈ ምርት ባከማቹና ሌሎች የመንገድ መብት ጥሰቶች በፈፀሙ አካላት እርምጃ ወስጃለሁ ብሏል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በተሽከርካሪ ግጭት ምክንያት ጉዳት የደረሰበትን የመንገድ ሀብት በመጠገን ላይ እንደሚገኝ በስራ አፈፃፀሙ ገልጿል።
