17.5 ሚሊዮን ዶላር ባጀት ተመድቦለታል
ሩዋንዳ በ17.5 ሚ. ዶላር በአፍሪካ የመጀመሪያውን የኤአይ ማበልፀጊያ ማዕከል ልታቋቁም መሆኑ ተዘገበ፡፡
የቢልና ሜሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን 17.5 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት በማድረግ፣ የሩዋንዳ ኤአይ ማበልፀጊያ ማዕከልን ለማቋቋም የተዘጋጀ ሲሆን፤ ሩዋንዳም የአፍሪካ የመጀመሪያዋ የኤአይ (AI) ማበልፀጊያ ማዕከል ልትሆን ነው ተብሏል፡፡
ኢንቨስትመንቱ ሩዋንዳ የአፍሪካ ቀጣይ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሃይል ለመሆን ትልቅ እርምጃ እንድትወስድ የሚያስችላት ሲሆን፤ ዋናው ትኩረትም በጤና፣ በግብርና እና በትምህርት ዘርፎች የኤአይ ፈጠራዎችን ማበልጸግ እንደሆነተጠቁሟል።
