በሱዳን በተፈጸመ ጥቃት ህጻናት ተገደሉ

Date:

ከሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ በምትገኘው ኦምዱርማን ከተማ ውስጥ በሱዳን ፈጥኖ ደርሽ ሃይሎች በደረሰ ጥቃት ቢያንስ ሶስት ህጻናት ሲሞቱ 4 ሰዎች መቁሰላቸው ተገለፀ።

እንደዥንዋ ገለጻ ሃጻናቱ የተገደሉት የታጣቂ ሃይሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ባደረሰት ጥቃት ነው፡፡

የሱዳን ዶክተሮች ኔትወርክ የተባለ የበጎ ፈቃደኞች ቡድን ባወጣው መግለጫ ታጣቂ ሃይሉ ሰላማዊ ዜጎች በተለይም ሴቶች እና ህጻናት በሚበዙበት አከባቢ ጥቃት መሰንዘሩ አለማቀፍ የጦርነት ህጎች መጣስ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በቅርብ ቀናት ውስጥ አር ኤስ ኤፍ በሱዳን ጦር ሃይሎች ቁጥጥር ስር ባሉ ወታደራዊ ቦታዎች እና ወሳኝ መሰረተ ልማቶች ላይ የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃቶችን ማድረስ አጠናክሮ ቀጥሏል።

ሱዳን ከሚያዝያ 2023 አጋማሽ ጀምሮ በሱዳን ወታደራዊ ሃይሎች  እና በአር ኤስ ኤፍ መካከል አስከፊ ግጭት ውስጥ ገብታ የነበረች ሲሆን ይህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ህይወቶችን የቀጠፈ ነው፡፡

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከ15 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በሱዳን ውስጥም ሆነ ከውጪ ተፈናቅለዋል ማለቱንም ዥንዋ ዘግቧል።

(ሀገሬ ቴቪ)

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...