በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1 ሺህ 655 ኢትዮጵያውያን መካከል የመጀመሪያዎቹ 320 ተመላሾች አዲስ አበባ ገብተዋል።
በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርሃኑ ጸጋዬ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
ይህ ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት በሪያድ የሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና በጂዳ የሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤት በቅንጅት ባከናወኑት ጥረት የተመዘገበ መሆኑ ተገልጿል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞም መንግሥት ኅብረተሰቡ በሕገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች የሐሰት የማህበራዊ ሚዲያ ማታለያዎች ሳይደለል ከሕገወጥ የውጭ ሀገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ ጥሪ አቅርቧል።
ዜጎችን ለከፍተኛ ችግር የሚዳርጉ ሕገወጥ ደላሎችን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩት የተቀናጁ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መረጃ አረጋግጧል።
