በተማሪ ቁጥር ልክ መጻሕፍትን ገዝቶ ያላዳረሰ ት/ቤት ካለ የእውቅና ፈቃዱ ይሰረዛል

Date:

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ትምህርት ቢሮ በከተማዋ የሚገኙ የግል ትምህርት ቤቶች በተማሪዎቻቸው ቁጥር ልክ መጻሕፍትን ገዝተው ማሰራጨት ካልቻሉ የእውቅና ፈቃዳቸው እስከመሰረዝ የሚደርስ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል።

የቢሮው ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ” በግል ትምህርት ቤቶች አልፎ አልፎ የሚታየው የመጻሕፍት እጥረት ከህትመት ጋር በተገናኘ ምክንያት እጥረት ኖሮ ሳይሆን ገዝተው ለተማሪዎቻቸው ማሰራጨትን እንደ ወጪ እና እንደ ድካም ስለሚያስቡት ነው ” ብለዋል።

ሃላፊው ይህን ያሉት በአዲስ ቲቪ በተላለፈ ” በጠረጴዛ ” በተሰኘ ፕሮግራም ላይ በቀረቡበት ወቅት ነው።

” የመማሪያ መጻሕፍት በበቂ ሁኔታ ታትመዋል?በተለይ በግል ት/ት ቤቶች ለተወሰነ ጊዜ መጻሕፍት ሽያጭ ይከናወን እና አልቋል ይባላል ይህ ለምን ሆነ ? ” የሚል ጥያቄ ለትምህርት ቢሮ ሃላፊው ቀርቦላቸው ነበር።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ምን መለሱ ?

” በተለይ አዲሱ ስርአተ ትምህርት ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በልዩ ሁኔታ ድጋፍ ተደርጎ ለተማሪዎቻችን አንድ ለአንድ እንዲደርስ ተደርጎ ህትመቱ በበቂ ሁኔታ ተሰራጭቷል።

የመጻሕፍት ህትመት እና ስርጭት ላይ ለመንግሥት ተማሪዎች መጻሕፍት በነጻ ይሰጣል ለግል ትምህርት ቤቶች በሪቮልቪንግ ፈንድ 250 ሚሊየን ተፈቅዶልን ይህንን ስራ እየሰራን እንገኛለን።

የግል ትምህርት ቤቶች ላይ ያለው ችግር ከተማሪዎች የመጽሐፍ ገንዘብ ሰብስበው ከትምህርት ቢሮ ስቶር ገዝተው ትምህርት ቤታቸው ማድረስ እና ማሰራጨት እንደ ትልቅ እዳ ነው የሚቆጥሩት ።

እንደከተማ ግን በቂ ህትመት ታትሞ ስቶራችን ሙሉ ነው ችግሩ ት/ቤቶች መጻሕፍቶቹን ከስቶር ወስደው ለተማሪዎች ማከፋል ላይ ነው ያለው።

በተለይ የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን ፈቃድ የሚሰጠው አካል እሱ ስለሆነ መጻሕፍት በተማሪዎቻቸው ቁጥር ልክ ወስደው ለተማሪዎቻቸው ያላዳረሱ ትምህርት ቤቶች ካሉ እውቅና ፈቃዳቸው እንዲሰረዝ ተግባብተናል።

በቂ መጻሕፍት አለን በግል ት/ቤቶች እየተሰራጨ ነው አሁንም በስርጭት ላይ ነው የሚገኘው ችግሩ ያለው ትምህርት ቤቶች ላይ ነው እንደ ወጪ እንደ ድካም ስለሚያስቡት ነው።

ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ትምህርት ቤቶችን በደንብ መመልከት እንጀምራለን በተማሪ ቁጥር ልክ መጻሕፍትን ገዝቶ ያላዳረሰ ት/ቤት ካለ የእውቅና ፈቃዱ ይሰረዛል።

አንድም ተማሪ ያለ መጽሐፍ መማር የለበትም ይሄንን አንታገስም ይህም የእርምጃችን አንዱ አካል ይሆናል ” ብለዋል።

Via tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...