በአለም ላይ ከ6 መቶ ሚሊየን በላይ ሴቶች በግጭት አከባቢዎች እንደሚኖሩ አንድ ጥናት ጠቆመ

Date:

በመጋቢት ወር በተደረገ ጥናት የፆታ እኩልነት ስጋት 60 በመቶ መጨመሩንና ከአራት ሀገራት አንዱ የሴቶችን መብት የመፃረር አዝማሚያ እንደሚያሳይ ተገልጿል፡፡

ከ 6 መቶ ሚሊየን በላይ ሴቶችና ልጃገረዶች አሁንም በግጭት ቀጠናዎች አካባቢ እንደሚኖሩ እና ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት መጨመሩንም ጠቁሟል።

እንደዚህ ያሉ ክስተቶች ባለፉት አመታት የተገኙ ስኬቶችን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብሏል ሪፖርቱ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴቶች አስራ አምስተኛ አመቱን ሲያከብር በዓለም ዙሪያ ያሉ ከአራት ቢሊየን በላይ ሴቶች እና ልጃገረዶች የፆታ እኩልነት ዉስጥ እንዲካተቱ ለማድረግ እንደሚሰራ አስታዉቋል፡፡

የሴቶችን መብት የሚፃረር እንቅስቃሴን መዋጋት ፣የሰላም ግንባታ ጥረቶችን መጨመር ፣ ሴቶች በሰላም ንግግሮች ላይ እንዲሳተፉ ማድረግ ፣ የኢኮኖሚ አለመመጣጠንን መፍታት የዕቅዱ አካል ሲሆን፤ ፆታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መቃወም እና  የሴቶችን የትምህርት ፣ የጤና እና የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋት ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሏል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሴቶች/ዩኤን ዉሜን/ ለፆታ እኩልነት ተጨማሪ ኢንቨስትመንት አስፈላጊ መሆኑን በመግለፅ፤ የመንግስት እና የግል ሴክተሮች ለሴቶች መብት ድጋፍ የሚሰጡትን የገንዘብ ድጋፍ እንዲጨምሩ አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...

ፈረንሳይ የ54 ነጥብ 6 ሚሊዮን ዩሮ ብድር ለመስጠት ተስማምታለች

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ሀገራቸው ለኢትዮጵያ የኃይል...