በአዲስ አበባ የባቡር ትራንስፖርት ትኬት ሽያጭ በዲጂታል መልኩ ሊጀመር ነው

Date:

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት ከወረቀት ትኬት ሽያጭ ወደ ዲጂታል ሽያጭ አገልግሎት ሊሸጋገር መሆኑን ገልጿል።

የዲጂታል ትኬት ሽያጩ ለጊዜው በተመረጡ ቦታዎች ማለትም በሀያት፣ጦርሀይሎች ዳግማዊ ሚኒሊክና ቃሊቲ ጣቢያዎች እንዲሁም በስታዲየም የሽያጭ ቁጥጥር በማድረግ የሚተገበር ይሆናል ተብሏል፡፡

የክፍያ ሥርዓቱ በቴሌ ሱፐር አፕና በዩኤስ ኤስዲ (USSD) ኮድ አማካኝነት መቁረጥ የሚያስችል ነው።

ይህ የፓይለት ሙከራ ድርጅቱ የወረቀት ሽያጭን ሙሉ ለሙሉ በማስቀረት ወደ ዲጂታላይዝድ የክፍያ ስርዓት ለመሸጋገር ለሚያደርገው ስራ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን የድርጅቱ የበላይ አመራሮች ተናግረዋል።

በዲጂታል ሽያጭና ቁጥጥር ለሚሳተፉ ሰራተኞች በሁለት ዙር ስልጠና የተሰጠ ሲሆን የፓይለት ሙከራው በቅርቡ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት አስታውቋል።

ባለፉት 10 አመታት ደንበኞች በተዘጋጁት 39 የትኬት መቁረጫ ጣቢያዎች የወረቀት ትኬት በመግዛት የቀላል ባቡሩን አገልግሎት ሲያገኙ እንደነበር ተመላክቷል።

ቀዳሚ ጽሑፍ
ቀጣይ ጥሑፍ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከ989 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከግንቦት 27 እስከ ሰኔ 3 ቀን 2018...

“እኔ እስካለሁ ድረስ ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት አትሆንም!”

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናንት ሰኔ 5 ቀን...

አገር እንዲህ ዓይንህን ለአፈር ይባላል?

በተጀመረው የአለም ዋንጫ ደቡብ አፍሪካ በሜክሲኮ መሸነፏን ተከትሎ አፍሪካ...

አሜሪካ እና ኢራን የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት በ24 ሰዓት ውስጥ እንደሚፈራረሙ ፓኪስታን አስታወቀች

ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን በሰላም ድርድሩ ማዕቀፎች ላይ መስማማታቸውን...