ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ያላትን ዝግጁነት ለዓለም የምታበስርበት 4ኛው “በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ ፎረም በመጋቢት ወር አጋማሽ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከገንዘብ ሚኒስቴርና ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር መጋቢት 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሚያካሂደው በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ፣ ከ800 በላይ ዓለም አቀፍ ባለሀብቶች፣ የንግድ መሪዎችና ፖሊሲ አውጪዎች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ኮሚሽነር ዶክተር ዘለቀ ተመስገን እንደገለጸው በባለፈው 3ኛው ፎረም በማዕድንና በሶላር ኢነርጂ ዘርፍ የተሰማሩ አምስት ድርጅቶች በ1.6 ቢሊየን ዶላር ስምምነት ተፈራርመው በአሁኑ ወቅት ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ የገቡ ሲሆን፤ በዘንድሮው 4ኛው ፎረም ደግሞ ከ2.6 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ የሚያወጡ አዳዲስ የኢንቨስትመንት ስምምነቶች እንዲፈረሙ እቅድ ተይዟል።
ይህ ፎረም የንግድ ለንግድ ትስስርን ከመፍጠር ባለፈ፣ ኢትዮጵያ ለውጭ ኢንቨስትመንት ያላትን ምቹ የፖሊሲ ከባቢና የልማት ዕድሎች ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተግባር የምታሳይበት ወሳኝ መድረክ እንደሚሆን ይታመናል።
“በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ” ዓለም አቀፍ ፎረም ሊካሄድ ነው
Date:
