በኢትዮጵያ የሲቪል ምዝገባ ስርዓትን ዲጅታላይዝ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

Date:

በመላ ሀገሪቱ የሲቪል ምዝገባን ወጥ ለማድረግ የቴክኖሎጅ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር አማካሪ አቶ ተስፋየ ወልዴ አስታውቀዋል።

በዋና ዳይሬክተር አማካሪ የተመራ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ልዑክ የኢትዮጵያ የሲቪል ምዝገባና ስታትስቲክስ መረጃ ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ በናሚቢያ ዊንድሆክ ይገኛል።

የናሚቢያ የሀገር ውስጥ ጉዳይ የኢሚግሬሽና ደህንነት ሚኒስትር ሉሲያ ኢፑምቡ የልዑካን ቡድኑን በቢሯቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን እንደ አህጉር እጅ ለእጅ ተያይዘን የሲቪል ምዝገባን እና ሌሎች ግቦቻችንን ተግባራዊ ለማድረግ በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአሁኑ ወቅት ምዝገባውን ከማንዋል /ወረቀት/ ወደ ዲጂታል መመዝገቢያ ሥርዓት ለማሸጋገር እና ለማዘመን ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል ያሉት የዋና ዳይሬክተር አማካሪው በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገውን ግምገማ ተከትሎ የአምስት አመት የCRVS ስትራቴጂክ እቅድ የተዘጋጀ ሲሆን በዚህ ረገድ የሲቪል ምዝገባ ሥርዓትን ዲጂታይዝ በማድረግ ላይ አስደናቂ እድገት ያስመዘገበች አገርን የስኬት ተሞክሮዎች መማር ለእኛ ጠቃሚ ነው ብለዋል።

አክለውም የጉብኝቱ ዋና ዓላማ የዲጂታል ሲቪል ምዝገባ እና የማንነት ስርዓቶችን በማስተዳደር ረገድ ስኬታማ ስልቶችን ለመውሰድ እንደሆነ በመግለፅ ለፈጣን ምላሻቸውና ለተደረገላቸው አቀባበል በተቋሙ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።

ናሚቢያ በዘርፉ ያላትን ምርጥ ተሞክሮ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና አተገባበር ላይ ያስመዘገበችውን ስኬት፣ ያጋጠማትን ተግዳሮትና ፈተናዎችን የተወጣችበት መንገድ በሚመለከት ገለፃ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ልዑኩ የከተማና የገጠር የሲቪል መመዝገቢያ ጽ/ቤቶችን፣ የካቱታራ ግዛት ሆስፒታል ፣ የዊንድሆክ ፖሊስ እና የናሚቢያ ፖሊስ ፎረንሲክ ላብራቶሪን ጎብኝቷዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከተማዋ ከ24 ሺህ በላይ ንቁ የግንባታ ፈቃድ ያላቸው ሳይቶች መኖራቸው ተገለፀ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ የሚደርሰውን የህይወትና የንብረት ጉዳት ለመቀነስ የቁጥጥርና የግንዛቤ...

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ለሕክምና በወሰደችው መድኃኒት ምክንያት ከውድድር ታገደች

የቀድሞዋ የሁለት ጊዜ የዓለየቀድሞዋፒዮኗ ኢትዮጵያዊቷ ጉዳፍ ፀጋይ ከውድድር በፊት...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እውቅና ሊሰጣቸው ነዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እውቅና የሚያገኙት የጎርጎርጎረሳዉያኑ 2026 በሞሮኮ...