በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን በጠና መታመም

Date:

ሰኞ ዕለት ታስረውበት ወደ ሚገኙበት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሄደው እንደጎበኋቸው የገለጹት ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ፣ አቶ ክርስቲያን በቅርቡ ቀዶ ሕክምና ከማድረጋቸው ጋር በተያያዘ ሕመማቸው እየተባባሰ መምጣቱን ገልጸዋል።

የአቶ ክርስቲያን ታደለ አንድ ቤተሰብ አባልም፣አቶ ክርስቲያን ከወራት በፊት በመቅረዝ ሆስፒታል ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን እና በቂ ክትትል ሳይደረግላቸው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲመለሱ መደረጋቸው አሁን ላሉበት ሁኔታ እንዳበቃቸው ተናግረዋል።

አቶ ክርስቲያን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄን (አብን) ወክለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እንዲሁም በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነበሩ።

በአማራ ክልል የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገ በኋላ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ በእስር ላይ እያሉ ያለመከሰስ መብታቸው ተነስቶ ላለፉት ሁለት ዓመታት በእስር ላይ ይገኛሉ።

ፍርድ ቤቶች ለዕረፍት ዝግ በመሆናቸው ብዙም እንደማይገናኙ የተናገሩት ጠበቃቸው ሰለሞን ደህና አለመሆናቸውን ከሰሙ በኋላ ወደ ማረሚያ ቤት ሄደው አቶ ክርስቲያንን ባገኟቸው ጊዜ በእጅጉ ታመው እና ደክመው መመልከታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።


ጠበቃው አክለውም ቀዶ ሕክምና ካደረጉ በኋላ ክትትል እና ምግብን ጨምሮ አስፈላጊውን እንክብካቤ በተገቢው ሁኔታ አለማግኘታቸው በጤና ሁኔታቸው ላይ ተጽእኖ እንዳለው አመልክተዋል።

አቶ ክርስቲያን ከወራት በፊት ቀዶ ሕክምና ተደርጎላቸው እንደነበር ቤተሰቦቻቸው እና ጠበቃቸው የገለጹ ሲሆን፣ በወቅቱ በተገቢው ሁኔታ ክትትል አግኝተው ሳያገግሙ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርገዋል ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ቅሬታ አሰምተው ነበር።


የአቶ ክርስቲያን ቤተሰቦች እንደሚሉት አቶ ክርስቲያን ያሉበት ሁኔታ አሳሳቢ ሲሆን ለመንቀሳቀስ እና ጠያቂዎችን ለማናገር አዳጋች በሆነ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ።


በተጨማሪም “ወደ ማረሚያ ቤቱ ከተመለሰ በኋላም ለማገገም የሚያስፈልገው እንደ አጥሚት እና ሌሎች ነገሮችን ይዘን እንዳንገባ ተከልክለናል። ከአንድም ሁለት ጊዜ አጥሚት ይዘን ተመልሰናል። በጣም ነው የታመመው፤ በሥርዓት እንኳን ቆሞ አያናግረንም።”


የቤተሰቡ አባል የሆኑት ግለሰብ አቶ ክርስቲያን ሕክምና እንዲያገኙ እና ያሉበት ሁኔታ እንዲሻሻል የሰብዓዊ መብት አካላት “የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈፀመባቸው ነው” ያሏቸውን እስረኞች እንዲጎበኙ ጠይቀዋል።


ዐቃቤ ሕግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል በሆኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና ሌሎችም ግለሰቦች ላይ ክስ የመሠረተው ከአንድ ዓመት በፊት መጋቢት 2016 ዓ.ም. ነበር።


አቶ ክርስቲያን የወንጀል ሕጉን እና የሽብር ወንጀልን ለመቆጣጣር እና ለመከላከል የወጣውን አዋጅ በመተላለፍ የተፈጸመ “ወንጀልን” እና የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን በመተላለፍ ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ነው።


ከሌሎች ተከሳሾች ጋር በቀረበባቸው ክስ ዐቃቤ ሕግ ምስክሮችን ማሰማት የጀመረ ሲሆን፣ በመጪው ጥቅምት 10/ 2018 ዓ.ም. ጉዳያቸው መታየት ይቀጥላል።

ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...