ብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ ምርቶቹን ወደ አለም አቀፍ ገበያዎች ሊያስፋፋ ነዉ

Date:

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የብሔራዊ የአልኮልና አረቄ ፋብሪካ ምርቶቹን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያዎች በማስፋፋት ሽያጩን እንዲያሳድግ መክሯል።

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ እንዳስታወቀው፣ ፋብሪካው ዕድገቱን ማስቀጠል እንዲችል የግብይት ሥራዎችን ማጠናከር፣ ወደ ውጭ ገበያ መግባትና የሀገር ውስጥ የስርጭት መረቡን ማሻሻል ይኖርበታል ብሏል።

በተጨማሪም፣ የፋብሪካውን ምርታማነትና የማምረት አቅም በማሳደግ እንዲሁም ገቢ የሚያስገኙ ንብረቶችን በአግባቡ በመጠቀም ትልቅ ዋጋ መፍጠር እንደሚችል አስረድቷል።

ይህ የተባለው የፋብሪካው 2017 በጀት ዓመት አፈፃፀሙ በተገመገመበት ወቅት ነዉ። መንግስታዊዉ ኩባንያው በዓመቱ ከታክስ በፊት 340 ሚሊዮን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ሲደርስ፣ አጠቃላይ ገቢው ደግሞ 2.6 ቢሊዮን ብር መሆኑም ተመላክቷል።

CapitalNews

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት 83,000 ህፃናት ተወልደዋል

ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ዘግይተው...