የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ዋና ጸሐፊ ዶክተር ቀነኒሳ ለሚ (ተባባሪ ፕሮፌሠር) ከኦሮ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ዋና ስራ አሥፈጻሚ ዶክተር ኢንጅነር መሣይ ዳንኤል ጋር ተወያዩ።
የሥራ ኃላፊዎቹ ሁለቱ ተቋማት በትብብር እና በጋራ በሚሠሩባቸው ዘርፎች ላይ መክረዋል።
ኦሮ ኮንስትራክሽን ግሩፕ በግንባታው ዘርፍ ያለውን አቅም በማጎልበት ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር በአቅም ግንባታ ሥልጠና እና በሌሎችም ዘርፎች በትብብር እንደሚሠራ ተጠቁሟል።
ምክር ቤቱም በተለይም በቢዝነስ ሊደርሺፕ አካደሚ የሥልጠና ማዕከሉ በኩል ሠፊ የሥልጠና እድል እንዳለውና ከግሩፑ ጋር መሥራት እንደሚፈልግም ተገልጿል።
