ትግራይ ክልል ውዝፍ ደሞዝ ለመክፈል 20 ቢልዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

Date:

የመንግሥት ሠራተኞችን ውዝፍ ክፍያ ለመክፈል 20 ቢልዮን ብር እንደሚያስፈልገው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ። ውዝፍ ደመወዝን በአንድ ጊዜ መክፈል እንደማይችል የገለፀው ጊዜያዊ አስተዳደሩ፤ ከአዲሱ በጀት ዓመት ቢያንስ አምስት በመቶውን ለውዝፍ ደሞዝ መክፈያ ለማዋል መወሰኑ አመልክቷል።

ትግራይ ክልል የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች በጦርነቱ ወቅት ያልተፈጸመው የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ እንዲከፈላቸው በተደጋጋሚ ያነሳሉ፤ ሆኖም እስካሁን ይህ ጉዳይ መፍትሔ አላገኘም።

የትግራይ ክልል መምህራን ማሕበር ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ወስዶት ችሎቱ የፌደራል መንግሥት የ12 ወራት፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ደግሞ የአምስት ወራት ውዝፍ ደመወዝ ለመምህራኑ እንዲከፍሉ ፈርዷል።

ሆኖም የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ግዚያዊ አስተዳደር ከፍርዱ በኋላ የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄዎች ፍርድ ቤቶች አቤት እንዳይባልባቸው የሚከለክል ደንብ ማውጣቱ ተሰምቷል። በዚህም ምክንያት ደንቡ እንዲሻር እንዲሁም ፍርዱ ተግባራዊ እንዲደረግ የትግራይ መምህራን ማሕበር የፍርድ ቤት ክርክሩ ቀጥሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ነው ትናንት በመቐለ በተጀመረው የትግራይ ትምህርት ጉባኤ ላይ የተገኙ መምህራን ለውዝፍ ደመወዝ ጥያቄያቸው ቁርጥ ያለ ምላሽ መንግሥት እንዲሰጥ የጠየቁት።


ከፍተኛ የበጀት እጥረት እንዳለበት የሚገልፀው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፥ ከፌዴራሉ መንግሥት የሚያገኘውን የበጀት ድጎማ ሙሉበሙሉ ለደመወዝ እና ሥራ ማስኬጃ እያዋለ መሆኑ ይገልፃል።

50 ሺህ ገደማ የሚገመቱ መምህራን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ120 ሺህ በላይ ለሚሆን በትግራይ ክልል ለሚገኝ መንግሥት ሠራተኛ የ17 ወራት ውዝፍ ደመወዝ ለመክፈል 20 ቢልዮን ብር እንደሚያስፈልገው ማስታወቁን ሚሊየን ኃይለሥላሴ በላከው ዜና ጠቅሷል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

” ከ140 በላይ ጠጠር አምራች ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ቆመዋል ” – ማህበሩ

" ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ። ግን መሬቱ መቼ እንደተወሰደባቸው...

ትራምፕ “በኢራን ላይ ሊፈጸም ታቅዶ የነበረውን ጥቃት አንፈጽምም” አሉ

ትራምፕ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ ቁልፍ የአሜሪካ አጋር ሀገራት መሪዎች...

በነዳጅ ጭማሪ በኬንያ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ የአራት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በኬንያ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ በዋና ከተማዋ ናይሮቢ በጸጥታ...

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት 83,000 ህፃናት ተወልደዋል

ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ዘግይተው...