የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ አመራሮች በቻይና የሻንሺ ግዛት ውጪ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኋንግ ዬንግ የተመራ ልዑክን ተቀብለው አነጋግረዋል።
በዚሁ ጊዜ ቻይና በኢትዬጵያ የሠው ሀብት ልማት ውስጥ ያላትን አበርክቶ ለማጠናከር እንደሚሠራ በቻይና የሻንሺ ግዛት ውጪ ጉዳይ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ኋንግ ዬንግ ገልጸዋል።
በምክትል ቢሮ ሀላፊው የተመራው የግዛቲቲ ልዑክ ከትምህርት ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች ጋር ውይይት ያደረገ ሲሆን በሠው ሀብት ልማት ዙርፍ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሠው ሀይል ግንባታ ትብብር ለማሳደግ ፍላጎቶ ያለ መሆኑን በሁለቱ ወገኖች ተገልጿል።
በቀጣይ በሚደረግ ግንኙነት በተማሪዎችና መምህራን ልውውጥ፣የትምህርት መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትና በመደገፍ እንዲሁም ነጻ የትምህርትና ስልጠና እድሎችን በማመቻቸት ረገድ አብሮ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዬች ላይ ውይይት ተደርጎል።
የሻንሺ ግዛት አስተዳዳሪ በቅርቡ በኢትዬጵያ የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ወቅት ቀጣይ በዉይይቱ እንደሚደረጉም ገልጿል።
