አንጋፋው የሙዚቃ ማናጀር አቶ አዲስ ገሠሠ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

Date:

ዓለም አቀፍ እውቅና የነበራቸው የሙዚቃ ማናጀር አቶ አዲስ ገሠሠ ባደረባቸው ሕመም በ73 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ አዲስ በአሜሪካ ሀገር በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ሰኔ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን ቤተሰቦቻቸው ለኢቢሲ ገልጸዋል።

በዓለም አቀፍ የሙዚቃ መድረክ ላይ ስማቸው በጉልህ ከሚነሣ ኢትዮጵያውያን አንዱ የሆኑት አቶ አዲስ፣ የቦብ ማርሌን ቤተሰብ የሙዚቃ ሥራዎችን በአስተማማኝነት ከመምራት ባለፈ፣ ዚጊ ማርሌን ከኢትዮጵያው ዳሎል ባንድ ጋር በማጣመር “ኮንሺየስ ፓርቲ” በተሰኘው አልበም የግራሚ ሽልማት እንዲያገኙ ትልቅ ታሪክ ሠርተዋል።

በሀገር ውስጥ የሙዚቃ ዕድገትም የጎላ አሻራ ያሳረፉ ሲሆን፣ ከታዋቂ ድምፃውያን ስኬቶች ጀርባ የነበሩ ቁልፍ ሰው ነበሩ።

በማኅበራዊ ሕይወታቸው ቀልድ አዋቂ፣ ተጫዋች እና ሰው አክባሪ እንደነበሩ የሚነገርላቸው አቶ አዲስ፣ ባለትዳር እና የአንድ ወንድ እና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ።

የአስከሬን ሽኝት እና የሥርዓተ ቀብር አፈጻጸም መርሐ-ግብር በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ቤተሰቦቻቸው አሳውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እስከ አምስት ዓመት እስራት የሚያስቀጡ የመረጃ ነጻነት አዋጅ ጸደቀ

ለ15 ዓመታት በስራ ላይ ከቆየው “የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት...

በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ማስጠንቀቂያ

በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኢምባሲ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ እየተከታተለና...

በበጀት አመቱ 22.9 ሚሊዮን ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ እየተሠራ ነው

ከታቀደው 22 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ኩንታል እስካሁን  20...

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...