አዋሽ ኢንሹራንስ በ2018 በጀት ዓመት ከፍተኛ እድገት በማስመዝገብ ማጠናቀቁን አስታውቋል። ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ከ6.1 ቢሊዮን ብር በላይ አረቦን ገቢ በማስመዝገብ፣ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ35 በመቶ እድገት እንዳለው ጠቁሟል።
ተቋሙ በሁሉም ዋና ዋና የስራ ዘርፎቹ ማለትም በሕይወትና ጤና ኢንሹራንስ እንዲሁም በተካፉል ኢንሹራንስ ዘርፎች የሀገር አቀፍ የገበያ መሪነቱን አስጠብቆ መቆየቱ ተገልጿል።
በተጨማሪም፣ በአጠቃላይ የግል መድን ዘርፍ ውስጥ ያለውን የመሪነት ቦታ ይበልጥ ማጠናከር መቻሉን አስታውቋል።
የአዋሽ ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ገመዳ፣ ይህ አስደናቂ ውጤት የኩባንያው ጠንካራ ስትራቴጂ፣ በሳል የአመራር ሥርዓት እና ቁርጠኛ የሰው ኃይል ጥምር ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
አዋሽ ኢንሹራንስ በአዲሱ የስራ ዓመት የገበያ መሪነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ የላቀ የደንበኛ አገልግሎት ለመስጠት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቋል።
